በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል ቸርነት ጉግሳን የግሉ አደረገ።
ወደ ዝውውር ገበያው የገባው መቻል አዲስ አሰልጣኝ ካመጣ በኋላ ያለፉትን ቀናት አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት የአብስራ ተስፋዬን ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱን ዘግበን ነበር። የአብስራ ወደ መቻል የሚያደርገውን ዝውውር የጨረሰ ሲሆን አሁን ደግሞ ቸርነት ጉግሳ የጦሩ አባል መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
የቀድሞ የወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው ቸርነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ቤት ቆይታ ያደረገ ሲሆን አሁን መዳረሻው መቻል ሆኗል።
ድህረገፃችን ሶከር ኢትዮጵያ አማካዩ ብሩክ ማርቆስ ወደ መቻል ለመግባት ከጫፍ መድረሱን ዘግበን የነበረ ሲሆን እሱም እንደ የአብስራ የመቻል ተጫዋች መሆኑ እርግጥ ሆኗል።