ከደቂቃዎች በፊት ቸርነት ጉግሳ፣ ብሩክ ማርቆስ እና የአብስራ ተስፋዬን የግሉ ያደረገው መቻል የግብ ዘቡን ውል ማራዘሙ ታውቋል።
አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ወደ ቡድኑ በማምጣት ለ2018 የውድድር ዘመን ራሱን እያጠናከረ የሚገኘው መቻል የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ካገባደደ በኋላ የአንድ ተጫዋች ውል ጎን ለጎን ማራዘሙን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።
ከመቻል ጋር ለመቀጠል ስምምነት የፈፀመው ተጫዋች የግብ ዘቡ ውብሸት ጭላሎ ነው። የቀድሞ የአዳማ ከተማ ተጫዋች የነበረው ውብሸት ያለፉትን ሦስት ዓመታት በመቻል ቤት ቆይታ አድርጎ የነበረ ሲሆን አሁንም ለተጨማሪ ዓመት በጦሩ ቤት ለመቆየት ከክለቡ ጋር ተስማምቷል።
