የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ቦሌ ክ/ከተማ የአሰልጣኞችን ውል ሲያራዝም በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ቦሌ ክ/ከተማ የአሰልጣኞችን ውል ሲያራዝም በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ካደጉበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የጸባይ ዋንጫ ማሸነፍ የቻሉት ቦሌ ክ/ከተማዎች 11 ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የ14 ነባሮችን እና የሁለቱን አሰልጣኞች ውል አራዝመዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ካለፉት ዓመታት አንጻር ተዳክመው በቀረቡበት የ2017 የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ካደረጓቸው 26 ጨዋታዎች 28 ነጥቦችን ሰብስበው 10ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ቦሌ ክ/ከተማዎች የፊታችን ነሐሴ 25 በሚጀመረው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክረው ለመቅረብ በቅድሚያ የዋና አሰልጣኛቸውን ቻለው ለሜቻ እና የረዳት አሰልጣኙን ኃይሌ ተስፉ ውል በማራዘም 11 አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የ14 ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል።

ቡድኑን የተቀላቀሉት  ግብ ጠባቂዋ ለይላ ሸሪፍ (ከንግድ ባንክ) ፤ ሰላማዊት ወንድወሰን (ከድሬዳዋ) ፣ ቤቲ ዘውዱ (ከባህር ዳር) ፤ ምሕረት አየለ እና ትዕግሥት ዮሐንስ ( ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ) ፤ አሰገደች ሸጎዬ ፣ ሄለን መንግሥቱ እና መስከረም ሙላት ( ከቂርቆስ ክ/ከተማ ) ፣ የዘርሃረግ ተካልኝ ( ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ) ፣ በላይነሽ ልንገረው ( ከልደታ ) ናቸው።

ቡድኑ በተጨማሪም የሜላት ጌታቸው ፣ መሰረት ዮሐንስ ፣ ፍቅርአዲስ ገዛኸኝ ፣ ሜላት አሊሙዝ ፣ ቃልኪዳን ሸዋነህ ፣ ጤናዬ ለታሞ ፣ ሊንጎ ኡማን ፣ ሚሊየን ጋይም ፣ ቤተልሔም ስለሺ ፣ መሰረት ባጫ ፣ ብዙነሽ ቡልቻ ፣ ዳሳሽ ሰውአገኝ ፣ ሜላት ደመቀ ፣ ፅግነሽ አዴን ውል ለተጨማሪ ዓመታት አራዝሟል።