አቤል ያለው ጦሩን ተቀላቅሏል

አቤል ያለው ጦሩን ተቀላቅሏል

የአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱ መቻል አቤል ያለውን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ካሳለፍነው ዓርብ ጀምሮ ወሳኝ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እያመጣ የሚገኘው መቻል እስካሁን ቸርነት ጉግሳ፣ የአብስራ ተስፋዬ፣ ብሩክ ማርቆስ እና መሀመድ አበራን ያስፈረመ ሲሆን የግብ ዘቡ ውብሸት ጭላሎ እና የሁለገቡን ተጫዋች ግሩም ሀጎስን ውል ማደሱም ይታወቃል። ከቀናት በፊት አጥቂው አቤል ያለውም መዳረሻው መቻል ቤት መሆኑን ዘገባ አቅርበን የነበረ ሲሆን ዝውውሩም እውን መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

የቀድሞ የሐረር ሲቲ፣ ደደቢት፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አቤል ወደ ግብፅ አምርቶ በዜድ ክለብ የእግርኳስ ህይወቱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ዳግም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለመቻል ፊርማውን አኑሯል።