የጣና ሞገዶቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል

የጣና ሞገዶቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል

ባህር ዳር ከተማ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ፈራሚዎቹን ከከፍተኛ ሊጉ አድርጓል።

የመስመር ተከላካያቸውን መሳይ አገኘሁ ውል በማደስ እንቅስቃሴ የጀመሩት ባህር ዳር ከተማዎች አጥቂውን ዮሐንስ ደረጄን ከድሬዳዋ ከተማ ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ከከፍተኛ ሊጉ የመስመር አጥቂ እና ተከላካይ አስፈርመዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ብሩክ ሰሙ ነው። ከዚህ ቀደም በመቻል ፣ ወልዋሎ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ሸገር ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቤንች ማጂ ቡና ተጫውቶ ያሳለፈው በአማካይነት እና በመስመር አጥቂነት የሚጫወተው ተጫዋቹ መዳረሻውን ባህር ዳር ከተማ አድርጓል።

ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለውን ተጫዋች በጅማ አባጅፋር የተጫወተው እና በተመሳሳይ ያለፈውን ዓመት በቤንች ማጂ ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ ማንያዘዋል ካሳ ሆኗል።