መቐለ 70 እንደርታዎች የአማካዩን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።
ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት መቐለ 70 እንደርታን ለማሰልጠን ከስምምነት እንደደረሱ መግለፃችን ይታወሳል ዛሬ ደግሞ ክለቡ በይፋዊ ገፁ አሰልጣኙ ክለቡን መረከባቸው ይፋ ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ የተስፈኛው አማካይ ኬኔዲ ገብረፃዲቕ ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ ያደረገው እና በ2016 ዓ.ም የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ክልል አቀፍ ሊግ ላይ ቡድኑ የውድድሩን አሸናፊ እንዲሆን ካስቻሉ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አማካዩ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ15 ጨዋታዎች ተሳትፎ 629′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።