ቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካዩን ውል ለተጨማሪ ዓመታት አራዝሟል።
አጥቂውን ቡአይ ኩዌት፣ አማካዩን አበባየሁ ዮሐንስ ፣ የመስመር ተከላካዩን መሳፍንት ጳውሎስን እና የመሃል ተከላካዩን ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤልን በማስፈረም የተገኑ ተሾመን ውል ያራዘሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሁን ደግሞ የአማካያቸውን አብርሃም ጌታቸውን ውል አድሰዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በ30 ጨዋታዎች ተሰልፎ 2358′ ደቂቃዎችን የተጫወተው አብርሃም ጌታቸው ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።
