ግብፅ ላይ በነበረው ጨዋታ በተፈጠረው ነገር ዙርያ ፌዴሬሽኑ ለፊፋ ያቀረበው አቤቱታ ከምን እንደደረሰ አቶ ባህሩ ተናግረዋል

ግብፅ ላይ በነበረው ጨዋታ በተፈጠረው ነገር ዙርያ ፌዴሬሽኑ ለፊፋ ያቀረበው አቤቱታ ከምን እንደደረሰ አቶ ባህሩ ተናግረዋል

👉”የብሔራዊ ቡድኑ ክብርን በሚነካ መልኩ የተደረገ ነው”

👉”የቅጣት ውሳኔውን የሚያሳውቀን ይሆንል።”


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብፅ ሽንፈት ባስተናገደበት ጨዋታ ወቅት በስታዲየም የሚገኙ የግበፅ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ባለበት እና በጨዋታው ወቅት በተደጋጋሚ ሌሰር ላይት በመደረጉ በወቅቱ ለፊፋ ቅሬታውን አሰምቶ ነበር። በዚህ ዙርያ አቶ ባህሩ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ምላሽ ሰጥተዋል

“በወቅቱ የተደረገው ነገር የሀገራችንን መገለጫ በሆነው ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ባለበት ሌሰር ላይት በማብራት እና ሌሎች ነገሮችን በማድረግ ክብርን በሚነካ መልኩ የተደረገ ነው። ቅሬታችን በጊዜው ለፊፋ ዲሲፕሊን ኮሚቴ አሳውቀናል። ፊፋም ሴፕቴምበር አስር ምላሽ እንደሚሰጠን በገለፀልን መሰረት ጉዳዮን በተመለከተ እንዳሳወቀን ከሆነ ‘ቅሬታው የጨዋታ ውጤት የሚያስቀይር እንዳልሆነ እና ሌሎች በዕለቱ የተፈጠሩ ነገሮችን ዲሲፒሊን ኮሚቴው በሂደት አካሄዱን ጠብቆ በግብፅ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ የቅጣት ውሳኔውን የሚያሳውቀን ይሆናል’ ብሎናል በማለት ተናግረዋል።”