አስቀድመን ባጋራናቹሁ መረጃ መሠረት አማካዩ ሀይደር ሸረፋ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል።
ከሦስት ክለቦች ጋር አራት የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለው የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ሀይደር ሸረፋ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለው የውል ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ በሻምፒዮኖቹ ቤት እንደማይቀጥል እና ቀጣይ ማረፊያው መቐሌ ሰባ እንድርታ ወይም የቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ ሊሆን እንደሚለች ገልፀንላቹ ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሰረት ሀይደር ሸረፋ በአዳማ ከተማ ለመጫወት መስማቱን አውቀናል።
በአማካይ ስፍራ ላይ በደደቢት ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ጅማ አባቡና የተጫወተው ሀይደር ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካሳካ በኋላ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ አምርቶ ለአራት ዓመታት ክለቡን በአምበልነትም ጭምር እየመራ በተከታታይ ሁለት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ካሳካ በኋላ በአዳማ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን አንድ ዓመት ከስድስት ወር በኢትዮጵያ መድን ቤት ቆይታ በማድረግ ቡድኑ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ የአንበልነት ሚናውን በአግባቡ በመወጣት በግሉ አራተኛ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ችሏል። አሁን ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ የሚመለስበትን ስምምነት መፈፀሙ ታውቋል።