ከሸገር ከተማ ጋር ተስማምቶ የነበረው በረከት ወልዴ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።
በሊጉ የመጀመርያውን ተሳትፎ የሚያደርገው ነገሌ አርሲ አሰልጣኝ በረከት ቱሉን በቡድኑ ካቆየ በኋላ ወደ ዝውውሩ በመግባት አስቀድሞ የዳዊት ተፈራ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ሀቢብ ከማልን ዝውውር ማጠናቀቁ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የአማካይ በረከት ወልዴን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን አውቀናል።
ለሸገር ከተማ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው በረከት የወላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን ፍሬ ሲሆን በወላይታ ድቻ ዋና ቡደን ከተጫወተ በኋላ ባለፉት አራት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት በነበረው ቆይታ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ሲታወቅ የወቅቱም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ተጫዋች ነው። አማካዩ አሁን መዳረሻው ሌላኛው አዲስ አዳጊ ክለብ ሆኗል።
