ለታሪካዊው አሰልጣኝ የዕውቅና መርሐግብር ሊዘጋጅ ነው

ለታሪካዊው አሰልጣኝ የዕውቅና መርሐግብር ሊዘጋጅ ነው

ሀገራችንን ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ያበቁት አንጋፋው አሰልጣኝ የምስጋና እና የዕውቅና መርሐግብር ሊደረግላቸው ነው።

“ለሀገራችን እግርኳስ ከ 42 ዓመታት በላይ በአሰልጣኝነት ብሔራዊ ቡድናችንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በማሰልጠን ፣ ለአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት በርካታ አሰልጣኞችን በማፍራትና በአሁኑ ወቅት ደግሞ ታዳጊዎችን በማፍራት ላይ የሚገኙት ተወዳጁ ሰው ጋሽ ሰውነት ቢሻው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናና ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል።” በሚል ይህንን ዓላማ ለማሳካት ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ይህ የምስጋናና ዕውቅና ስነ ስርዓት በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት በመሆኑ መርሐግብሩን በይፋ ለማስጀመር ማክሰኞ መጋቢት 29/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ጋዜጣዊ መግለጫ ቦሌ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ለመስጠት እቅድ መያዙን ሰምተናል።