በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ማሰናበቱ ታውቋል።

በዘንድሮ የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ31 ሳምንታት ጉዞ በአማካኝ በጨዋታ ከአንድ ነጥበረ በታች እያስመዘገበ 19ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው መቐለ 70 እንደርታ የውድድር ዓመቱን ከጀመሩት አሠልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ጋር ከተለያየ በኋላ በመንበሩ አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ሾሞ የነበረ ሲሆን ከአስጊው ቀጠና መውጣት አለመቻሉን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ከአሠልጣኙ ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

