የቀድሞ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ቢኒያም በላይ በይፋ የሲዳማ ቡና ተጫዋች ሆኗል።

በአፍሪካ መድረክ እና በሀገር ውስጥ ውድድሮች ለሚጠብቃቸው ጨዋታዎች ራሳቸውን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ የገቡት ሲዳማ ቡናዎች ከቀናት በፊት ቢኒያም በላይን ለማስፈረም መቃረባቸውን ገልፀን ነበር።
ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ ቢንያም ለሲዳማ ቡና ለሁለት ዓመት ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩን አውቀናል።
ሲዳማ ቡና ከዚህ ቀደም የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ያራዘሙ ሲሆን የቢኒያም በላይ ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀል ቡድኑ የበለጠ ያጠነክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

