የሲዳማ ቡና ወሳኝ ተጫዋቾች ለወሳኙ ጨዋታ ይደርሱ ይሆን  ?

የሲዳማ ቡና ወሳኝ ተጫዋቾች ለወሳኙ ጨዋታ ይደርሱ ይሆን ?

ትናንት ጉዳት ያስተናገዱት ሁለቱ የሲዳማ ቡና ቁልፍ ተጫዋቾች ለወሳኙ የቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታ ይደርሱ ይሆን የሚለውን ሶከር ኢትዮጵያ ማጣራት አድርጋለች።

በመጀመርያው የ2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን በሜዳቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽንፈት ያስተናገዱት ሲዳማ ቡናዎች በጨዋታው የመጀመርያ አስራ አምስት ደቂቃዎች አጥቂው መስፍን ታፈሰ እና አምበሉ ያሬድ ባየህን ጉዳት አስተናግደው ተቀይረው መውጣታቸው ይታወሳል።

ቀደም ብለን ሁለቱ ተጫዋቾች በሳምንቱ መጨረሻ ከሱዳኑ ክለብ አል ሂላል በድሬዳዋ ስታዲየም በሚደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ወሳኝ የማጣርያ ጨዋታ የመሳተፋቸው ጉዳይ አጣርተን እንደምናሳውቃቹሁ በገለፅነው መሠረት ተከታዮን መረጃ አግኝተናል።

የሁለቱም ተጫዋቾች ጉዳት ተመሳሳይ የጡንጫ መሳሳብ ህመም መሆኑ እንዲሁም ጉዳቱ አሳሳቢ እንደሆነ እና ለጨዋታው የመድረሳቸው ነገር ጠባብ እንደሆነ አረጋግጠናል። ሆኖም የህክምና ክፍሉ ከጨዋታው መዳረሻ በፊት ባሉት ቀናቶች ከህመማቸው አገግመው ለጨዋታው እንዲደርሱ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደረጉ አውቀናል።

ሶከር ኢትዮጵያ ቡድኑ ነገ ድሬዳዋ ከተማ ከገባ በኋላ በሚያደርገው ዝግጅት ላይ በሁለቱ ተጫዋቾች ዙርያ የሚኖሩ አዳዲስ ነገሮችን ተከታትላ ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል።