ዩጋንዳዊው ራሱን ከብሔራዊ ቡድን አገለለ

ዩጋንዳዊው ራሱን ከብሔራዊ ቡድን አገለለ

የሲዳማ ቡናው ተጫዋች ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉ ይፋ አደረገ

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲንጋዳ ብላክ ስታርስን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ የሚገኘው ዩጋንዳዊው አማካይ ካሊድ አውቾ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉ ይፋ አድርጓል።

ከ2013 ጀምሮ ሀገሩን መወከል የጀመረው እና በሀገሩ መለያ 77 ጨዋታዎች ማድረግ የቻለው ይህ የቀድሞ የክሬኖቹ አምበል በ2017፣ 2019 እና 2025 የአፍሪካ ዋንጫዎች ጨምሮ በቻን እና በሴካፋ ውድድሮች መሳተፍ የቻለ ሲሆን በዩጋንዳ ብሔራዊ በወጥነት ለበርካታ ዓመታት ካገለገሉ ተጫዋቾች በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

ከዚህ ቀደም በያንጋ አፍሪካንስ ፣ ምስር አል መቃሳ ፣ ሲምባ ፣ ጎር መሀያ እንዲሁም በሰርብያ ክለቦች ሬድ ስታር እና ኦ ኤፍ ኬ ብዮጋርድ ተጫውቶ በክለብ ደረጃ አምስት የሊግ ዋንጫዎች ጨምሮ በድምሩ አስራ ሁለት ዋንጫዎች ማንሳት የቻለው የተከላካይ አማካዩ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሑፍ የወቅቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርድዮቪች ሚሉቲንን አመስግኗል።