👉 አዲስ ትውልድ እየመጣ ነው በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ
👉 የነገውን ጨዋታ እናሸንፋል
👉 ሀገሬን በማገልገሌ በጣም ደስተኛ ነኝ

ሉሲዎቹ ለኦሎምፒክ ማጣርያ ነገ በድሬዳዋ ስታዲየም ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ላለባቸው የመልስ ጨዋታ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል አጥቂዋ ሎዛ አበራ በተለያዮ ጉዳዮች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሐን የሰጠችውን ማብራሪያ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
አስቀድማ ስለ ዘገየችበት ምክንያት ተጠይቃ ስትመልስ “ለብሔራዊ ቡድን መጠራቴ በክለቤ መረጃው ቢደርሰውም በፊፋ ህግ መሰረትን ነው መሄድ ያለብሽ በመባሌ ልዘገይ ችያለው። ያም ቢሆን ሐሙስ መጥቼ ከዓርብ ጀምሮ ቡድኑን ተቀላቅዬ እየሰራው እገኛለው። በዚህም ሀገሬን በማገልገሌ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች
የቡድኑ ስብስብን በተመለከተ ስትናገርም” ረጅም ዓመት ብሔራዊ ቡድን እንደ ቆየ ሰው ሆኜ ስናገር አሁን በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ያሉት ተጫዋቾች አብዛኛዎቹ አዲስ ናቸው። አዲስ ትውልድ እየመጣ ነው እነርሱም ለሀገራቸው ታሪክ መስራት የሚችሉ ልጆች ናቸው። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ” ካለች በኋላ “የነገውን ጨዋታን ማሸነፍ የሚያስችለን በቂ ዝግጅት አድርገናል ከእግዚአብሔር ጋር እናሸንፋለን” ብላለች
በመጨረሻም “የድሬዳዋ ህዝብ እንደሚታወቀው ለእግርኳስ ያለው ፍቅር የተለየ ነው። ነገ ህዝቡ ወደ ስታዲየም በነቂስ በመምጣት ከጎናችን እንዲሆን ጥሪዬን አስተላልፋለው” በማለት ንግግሯን አጠቃላለች።

