ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና 0-1 ሀዋሳ ከተማ
30′ አስቻለው ግርማ


* ጨዋታው እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡

– ዳኞች የሁለቱ ቡድን አምበሎችን እያነጋገሩ ይገኛሉ፡፡

– ተጫዋቾች ወደ ሜዳ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

– ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡ ጨዋታው መቀጠል አለመቀጠሉ አልታወቀም፡፡

– ተመልካቾች ሙሉ በሙሉ ከስታድየሙ ወጥተዋል፡፡ የስታድየመ መብራቶችም እየጠፉ ነው፡፡

– በረብሻው ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በአምቡላንስ እየተወሰዱ ነው፡፡

– ጨዋታውን ለመጀመር የኮሚሽነሩ እና የፀጥታ ሀላፊው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው፡፡

– የመጀመርያው አጋማሽ ከተጠናቀቀ ከ25 ደቂቃ በላይ ቢያልፍም ሁለተኛው አጋማሽ እስካሁን አልተጀመረም፡፡

– ወንበሮች እየተነቃቀሉ በመወርወር ላይ ይገኛሉ፡፡ ባነሮች እየተቀደዱ ሲሆን ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ከግርግር ለማምለጥ እየተተረማመሰ ይገኛል፡፡

– በሚስማር ተራ አካባቢ የሚገኙ ደጋፊዎች ከፀጥታ ሃይሎች ጋር እየተጋጩ ይገኛሉ፡፡ ግርግሩ በመላው የስታድየሙ ክፍለል ተዳርሶ ከፍተኛ ትርምስ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡

እረፍት!!
የመጀመሪያው አጋማሽ በሀዋሳ ከተማ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45+7′ ኤልያስ ማሞ የመታው ቅጣት ምት በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
45+5′
ፍርዳወቅ ሲሳይ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

45+3′ ሃይማኖት ወርቁ ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
45′
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 8 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

40′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ኤፍሬም በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ግርማ ከመስመር ላይ መልሶታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ወንድይፍራው በድጋሚ ቢሞክርም በተከላካዮች ተመልሷል፡፡

36′ ጨዋታው ከቆመበት ቀጥሏል፡፡

* ከግቡ መቆጠር በኋላ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ዘለው እየገቡ ይገኛሉ፡፡ ዳኛውን ለመምታት በመጋበዝ ላይም ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ሀዋሳ ከተማ
30′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ጋዲሳ ሲመታው አቅጣጫ ቀይሮ ወደ አስቻለው ሲያመራ አስቻለው ከመረብ አሳርፎታል፡፡

28′ አብዱልከሪም ወደኀላ የመለሰው ኳስ በማጠሩ ፍርዳወቅ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

25′ ጨዋታው በሞቀ ድጋፍ ፣ በተጋጋለ መንፈስ እና በጉሽምያ በታጀበ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

19′ ታፈሰ ሰለሞን ያሻገረውን ኳስ አስቻለው ሲሞክረው ወንድይፍራው ከመስመር አውጥቶታል፡፡ እጅግ ለግብ የቀረበ ሙከራ ነበር፡፡

14′ አብዱልከሪም የሞከረው ኳስ ኢላማውነን ስቶ ወጥቷል፡፡

10′ እስካሁን የግብ ሙከራ አልተመለከትንም፡፡ ቡናዎች ኳሱን መቆጣጠር ቢችሉም ወደ ሳጥኑ ለመግባት ተቸግረዋል፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


ኢትዮጵያ ቡና
1 ሀሪሰን ሄሱ

13 አህመድ ረሺድ – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን- 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 15 አብዱልከሪም መሀመድ

3 መስኡድ መሃመድ (አምበል) – 25 ጋቶች ፓኖም – 9 ኤልያስ ማሞ

24 አማኑኤል ዮሃንስ – 7 ሳዲቅ ሴቾ – 14 እያሱ ታምሩ


ተጠባባቂዎች
99 ወንድወሰን ገረመው
2 አክሊሉ ዋለልኝ
4 ኢኮ ፊቨ
18 ሳላምላክ ተገኝ
27 ዮሴፍ ዳሙዬ
14 ቶማስ እሸቱ
28 ያቡን ዊልያም


የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
18 ብርያን ቴቤጎ

2 ግሩም አሰፋ – 8 ግርማ በቀለ – 17 ሙጂብ ቃሲም – 7 ደስታ ዮሐንስ

24 ሃይማኖት ወርቁ – 21ሙሉጌታ ምህረት (አምበል)
13 አስቻለው ግርማ – 5 ታፈሰ ሰሎሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

27 ፍርዳወቅ ሲሳይ


ተጠባባቂዎች
1 ዮሃንስ በዛብህ
6 አዲስአለም ተስፋዬ
19 ዮሐንስ ሰገቦ
4 አስጨናቂ ሉቃስ
10 በረከት ይስሃቅ
15 መድሃኔ ታደሰ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *