ወላይታ ድቻ 1-1 መከላከያ
18′ አላዛር ፋሲካ (ፍቅም) | 38′ ቴዎድሮስ በቀለ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
88′ መሃመድ ናስር ወጥቶ ሳሙኤል ሳሊሶ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
86′ አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ ወንድማገኝ በለጠ ገብቷል፡፡
85′ ማራኪ የተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ አገባው ሲባል ተከላካዮች ተደርበው አወጡበት፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
77′ ሃይለየሱስ ብርሃኑ ወጥቶ መሳይ አንጪሶ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
76′ ፍሬው ሰለሞን ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡
70′ ጨዋታው በተጋጋለ መንፈስ እና ፈጣን እንቅስቃሴ እየተሟሟቀ ቀጥሏል፡፡
66′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ቶማስ በጭንቅላቱ በመግጨት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወጣ፡፡
የሚያስቆጭ አጋጣሚ
ቢጫ ካርድ
64′ አዲሱ ተስፋዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ሚካኤል ደስታም የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም የቢጫ ካርድ ተመዞበታል፡፡
60′ ከግራ መስመር የተሻገረለትን ግልጽ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ስንታየሁ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
የተጨዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
52′ ፀጋ አለማየሁ ወጥቶ ስንታየሁ መንግስቱ ገብቷል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ 1-1 ተጠናቋል፡፡
ጎልልል !!! መከላከያ
38′ ቴዎድሮስ በቀለ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር መከላከያን አቻ አድርጓል፡፡ ወላይታ ድቻ ከ9 ጨዋታ በኀላ ግቡ ተደፍሯል፡፡
35′ መከላከያዎች ወደ ጨዋታው የሚመልሳቸውን ጎል ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
31′ መሀመድ ናስር ወደ ግብ የመታውን ኳስ ወንድወሰን በቀላሉ ይዞበታል፡፡
30′ በርካታ ቁጥር ያለው ተመልካች በቦዲቲ ይገኛል፡፡ የስታድየሙ ድባብ ለጨዋታው ድምቀት በመሆን ላይ ይገኛል፡፡
25′ ሽመልስ ተገኝ ከአሰልጣኝ ገብረመድህን ጋር በጨዋታ እንቅስቃሴ መሃል ሰጣ ገባ ውስጥ እየገቡነው፡፡
ጎልልል!!! ወላይታ ድቻ
18′ አላዛር ፋሲካ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
ፍጹም ቅጣት ምት
17′ በድሉ ያሻማውን ቅጣት ምት ቴዎድሮስ በእጁ በመንካቱ የፍፁም ቅጣት ምት ለወላይታ ድቻ ተሰጥቷል፡፡
15′ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጎል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ወስነው አብዛኛው እንቅስቃሴያቸውን በመሀል ሜዳ ላይ ገድበዋል፡፡
9′ የመጀመርያ ሙከራ
አማኑኤል ከ16:50 ውጭ አክሮ የመታው ኳስ ለጥቂት አግዳሚውን ታኮ ወጣ፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀመረ::
የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
12 ወንደሰን አሸናፊ
9 ያሬድ ዳዊት – 3 ቶማስ ስምረቱ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 2 ፈቱዲን ጀማል
17 በዛብህ መለዮ – 8 አማኑኤል ተሾመ – 16 ሃይሀየሱስ ብርሃኑ – 18 በድሉ መርዕድ
12 ጸጋ አለማየሁ – 19 አላዛር ፋሲካ
ተጠባባቂዎች
1 መክብብ ደገፉ
5 ዳግም ንጉሴ
21 መሳይ አንጪሶ
23 ፀጋዬ ብርሃኑ
20 ስንታየሁ መንግስቴ
10 እንዳለ መለዮ
26 ወንድማገኝ በለጠ
የመከላከያ አሰላለፍ
1 ጀማል ጣሰው
2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ 6 ታፈሰ ሰርካ
26 ኡጉታ ኦዶክ – 21 በሃይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ
10 ፍሬው ሰለሞን – 17 መሃመድ ናስር – 19 ሳሙኤል ታዬ
ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
7 ማራኪ ወርቁ
11 ሙጃኢድ መሃመድ
29 ሙሉቀን ደሳለኝ
9 ሳሙኤል ሳለሊሶ
12 አቤል ከበደ
20 ካርሎስ ዳምጠው