ጋና 4-0 ኢትዮጵያ
6′ 75′ ያዎ ያቦሃ 9′ ዳውዳ መሃመድ 58′ ኢቫንስ ሜንሳህ
[ ድምር ውጤት 5-2 ]
(ጨዋታውን የምናስተላልፍላችሁ ከኤፍ ኤም 97.1 የቀጥታ ስርጭት እና ከተለያዩ ድረገፆች በምናገኘው መረጃ ነው)
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በጋና 4-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ጋና በድምር ውጤት 5-2 በመርታት ወደ ተከታዩ የማጣርያ ዙር አልፋለች፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ጋና
80′ ኒኮላስ ኦኮፑ ወጥቶ ኢሳክ ኮንዳ ገብቷል፡፡
77′ የቡድን መሪው ቾል ቤል ከዳኛው ጋር ውዝግብ ወስጥ ገብተዋል፡፡
ጎልል!!!
75′ ያው የቦሃ በቅጣት ምት 4ኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
74′ ተስፋዬ ሽብሩ በኢማኑኤል የቦሃ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ጋና
67′ አሞንዶ መሃመድ ወጥቶ ኢማኑኤል የቦሃ ገብቷል
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
66′ ሚካኤል ለማ ወጥቶ ኪዳኔ አሰፋ ገብቷል፡፡
ጎልልል!!!
58′ ኢቫንስ ሜንሳህ የጋናን 3ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
49′ ኪንግስሌይ ፎቢ ያሻማው ኳስ ቋሚውን ገጭቷል፡፡
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በጋና 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
42′ ጆናታን ኦሳቦቲ ጥሩ የማግባት አጋጣሚ መጠቀም አልቻለም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ጋና
41′ ኢሚኑኤል ሎሞቲ ወጥቶ ሚካኤል ኦቶ ገብቷል፡፡
40′ ዘላለም ኢሳያስ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
20′ ዳዊት ተፈራ ወጥቶ አቡበከር ሳኒ ገብቷል፡፡
18′ ያው ባህ ከርቀት የመታውን ኳስ ተክለማርያም አውጥቶታል፡፡
ጎልል!!!
9′ አምበሉ ዳውዳ መሃመድ የጋናን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ጎልል!!!!
6′ ያው ያቦሃ ለጋና የመጀመርያውን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
1′ በጨዋታው መጀመርያ ጋናዎች የመጀመርያ ሙከራቸውን አድርገው ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የጋና አሰላለፍ
1 ክዋሜ ባህ
5 ኪንግስሌይ ፎቢ – 3 ጂኦፍሬይ አቼምፖንግ – 2 ዳንኤል አሞሃ – 6 ኒኮላስ ኦፖኩ
4 መሃመድ አማንዶ – 17 ያው ያቦሃ – 14 ኢማኑኤል ሎሞቲ
18 ጆናታን ኦሳቡቴይ – 10 ዳውዳ መሃመድ (አምበል) – 11 ኢቫንስ ሜንሳህ
የኢትዮጵያ አሰላለፍ ፡-
1 ተክለማርያም ሻንቆ
8 እንየው ካሳሁን – 2 ሃይደር ሙስጠፋ – 6 ተስፋዬ ሽብሩ – 7 ደስታ ደሙ
16 ዘላለም ኢሳያስ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ (አምበል)
17 ዳዊት ማሞ – 11 ዳዊት ተፈራ – 15 ሚካኤል ለማ
9 አሜ መሃመድ