ፕሪሚየር ሊግ ፡ ኤሌክትሪክ ወሳኝ ድል ሲያስመዘግብ ዳሽን ወርቃማ እድሉን አሳልፎ ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ላለመውረድ የሚደረገው ትግል አጓጊ መልክን እንዲይዝ ያስቻሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ 11 እና 12ኛደረጃ ይዘው የተገናኙት ዳሽን ቢራ እና አርባምንጭ ከተማ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን ፈፅመዋል፡፡

የመጀመሪያው አጋማሽ ካለግብ በተጠናቀቀበት ጨዋታ ዳሽን ቢራዎች በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያ ደቂቃዎች በኤዶም ሆሶውሮቪ እና የተሻ ግዛው አማካኝነት አስቆጥረው 2-0 መምራት ቢችሉም አመለ ሚልኪያስ እና ተሾመ ታደሰ ያስቆጠሯቸው ግቦች ለአርባምንጭ ወሳኝ ነጥብ አስገኝቷል፡፡
ውጤቱ አርባምንጭ ከተማ 26 ነጥብ ይዞ ባለበት እንዲቆይ ሲያደርገው 24 ነጥብ የሰበሰበው ዳሽን ቢራን ወደ ወራጅ ቀጠናው መልሶታል፡፡

PicsArt_1466010203745

ወደ ድሬዳዋ ያቀናው ኤሌክትሪክ የ1-0 ድል አስመዝግቦ የወራጅ ቀጠናውን ለዳሽን ቢራ አስረክቧል፡፡ የኤሌክትሪክን ብቸኛ የማሸነፍያ ግብ ከመረብ ያሳረፈው ፍፁም ገብረማርያም ነው፡፡
ውጤቱ ባለፈው ሳምንት አስከፊ ሽንፈት ለደረሰበት ኤሌክትሪክ መጠነኛ እፎይታ የሰጠ ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ በሜዳው የተሸነፈው ድሬዳዋ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል፡፡
ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ደደቢት በዳዊት ፍቃዱ እና ሳሚ ሳኑሚ ግቦች ሁለት ጊዜ የመምራት እድል ቢያገኙም ሀዋሳ በአስቻለው ግርማ እና ሙጂብ ቃሲም (ፍጹም ቅጣት ምት) ግቦች አቻ መሆን ችለዋል፡፡ 
በጨዋታው የደደቢቱ አምበል ብርሃኑ ቦጋለ በሁለት ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ ካለ ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡

ሊጉ ሊጠናቀቅ 3 ጨዋታዎች ብቻ ሲቀሩት ቻምፒዮን ለመሆን ከቀጣይ ጨዋታ አቻ የሚበቃው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ48 ነጥብ ይመራል፡፡ 

ቀጣዮቹ 3 ጨዋታዎች ሀዲያ ሆሳዕናን ተከትሎ የሚወርደውን ክለብ ይለያል፡፡ ከወገቡ በታች ያሉ ክለቦች የመውረድ ስጋት ቢኖርባቸውም ከ11-13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት አርባምንጭ ፣ ኤሌክትሪክ እና ዳሽን ቢራ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1465999992685

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች

PicsArt_1466004558469

የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች 

ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2008

09፡00 አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (አዳማ)

እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2008

09፡00 ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)

11፡30 መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)

ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2008

09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ (አርባምንጭ)

09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዲያ ሆሳዕና (አአ ስታድየም)

10፡00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ዳሽን ቢራ (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *