ዳሽን ቢራ በዘንድሮው የውድድር ዘመን መጀመርያ በሾማቸው አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ እና ረዳታቸው በፍቃዱ ዘሪሁን ምትክ አሰልጣኝ ተገኝ እቁባይን በጊዜያዊነት መሾማቸውን አስታውቋል፡፡
ዳሽን ቢራ ባለፈው ሀሙስ በደደቢት የ4-1 ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ አሰልጣኝ ታረቀኝ እና ረዳታቸው ከክለቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት በመቋረጡና ያሉበትም ባለመታወቁ ለክለቡ ሪፖርት እንዲያደርጉ ከትላንት በስቲያ የተነገረ ቢሆንም ሪፖርት ማድረግ ባለመቻላቸው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንደተገደደ ክለቡ አስታውቋል፡፡
ጊዜያዊ አሰልጣኝ ተደርገው የተሾሙት ተገኝ አቁባይ የዳሽን ቢራ ተስፋ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ክለቡ ዛሬ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ነጥብ የተጋራበትን ጨዋታ መርተዋል፡፡
ዳሽን ቢራ በአሁኑ ወቅት በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በ25ኛ ሳምንት ከሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ እንደዛሬው ሁሉ አዳማ ላይ የሚያደርግ መሆኑ ከአሰልጣኝ ሹም ሽሩ ጋር ተደማምሮ የመውረድ ስጋቱን ያባባሰበት ሎኗል፡፡