FT
|
ኢትዮጵያ ቡና
26’ኤኮ ፊቨር |
1-0
|
ቅዱስ ጊዮርጊስ
– |
ተጠናቀቀ!!
ኢትዮጵያ ቡና በኢኮ ፊቨር ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፏል፡፡
የተጨዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
90+1′ ኤልያስ ማሞ ወጥቶ አብዱልከሪም ሀሰን ገብቷል።
ተጨማሪ ደቂቃ – 4
90′ የቡና ተጨዋቾች በተደጋጋሚ እየወደቁ ስለነበርየተጨመረው ደቂቃ ትንሽ ነው በማለት የጊዮርጊስ ደጋፊዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
86′ ኢትዮጵያ ቡናዎች ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው ሜዳ ላይ እየተከላከሉ ነው አሰልጣኝ ንቦሳ ቪሶቪችም በጭንቀት እየተንቆራጠጡ የቡድናቸውን መከላከል እየመሩ ነው፡፡
83′ ደጉ ደበበ በያስር ሙገርዋ ተቀይሮ መግባቱን ተከትሎ ምንተስኖት ወደ መሀል አማካይነት ሚና ከመጣ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጨዋታውን ይበልጥ ተቶጣጥረው ጫና እየፈጠሩ ነው።
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
82′ አማኑኤል ዮሀንስ በመጎዳቱ እና በህክምና እርዳታ ጨዋታውን መቀጠል ባለመቻሉ ወንድይፍራው ጌታሁን ተቀይሮ ገብቷል፡፡
75′ ኢትዮጰያ ቡናዎች በተጋጣሚያቸው እየደረሰባቸው ባለው ጭና እና ውጤቱንም ለማስጠበቅ በሚመስል መልኩ በብዛት በራሳቸው ሜዳ ላይ ሆነው በመከላከል በመልሶ ማጥቃት እየተጫወቱ ነው፡፡
የተጨዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
73′ ራምኬል ሎክ ሲወጣ ዘካሪያስ ቱጂ ገብቷል።
72′ ኤልያስ ማሞ በግምት ከ 30 ሜትር በቀጥታ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል፡፡
71′ አዳነ ግርማ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት ላይ ከመሬት የነጠረ ኳስ አክርሮ ሞክሮ በቡናዎች ጎል ቀኝ በኩል ወጥቶበታል።
70′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በራምኬል ሎክ የቀኝ መስመር ያደላ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው።
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
65′ ያቡን ዊልያም ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል።
63′ ሳልሀዲን ሌላ ኳስ ወደ ቡናዎች የግብ ክልል ይዞ በመግባት ቢሞክርም አሁንም ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡
62′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ አዳነ ግርማ ገብቷል።
61′ በግራ መስመር የተሰጠውን ቅጣት ምትም አበባው አሻምቶት ሳልሀዲን ሰይድ ከግቡ ጥቂት ሜትሮች ላይ ያገኘውን እድል በሚያስገርም መልኩ ስቶታል፡፡
ቢጫ ካርድ
60′ ኢኮ ፌቨር አቡበከር ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
58′ ያስር ሙጌርዋ ወጥቶ ደጉ ደበበ ገብቷል፡፡
54′ ኤልያስ ማሞ በግምት ከ20 ሜትር የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
53′ በሁለቱም በኩል ከመጀመርያው አጋማሽ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ደካማ እንቅስቃሴ እየታየ ነው፡፡
50′ እያሱ ታምሩ አቡበከር ሳኒን ጎትቶ በማስቀረቱ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ተጀመረ!!!
ሁለተኛው አጋማሽ ልተለመደ ሁኔታ ለምሩፅ ይፍጠር የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀመረ፡፡
እረፍት!!!
የመጀመሪያው አጋማሽ በቡና መሪነት ተጠናቋል፡፡
45+2′ አህመድ ረሻድ ኳስ ከግብ ክልሉ ለማራቅ ሲሞክር በአስቻለው ታመነ ጥፋት ተሰርቶበት ወድቋል።
ተጨማሪ ደቂቃ – 2
43′ ኢትዮጵያ ቡናዎች በቅዱስ ጊዮርጊሶች የጎል ክልል ላይ ኳስ በብዛት በመቀባበል ሰብረው ለመግባት እየሞከሩ ነው።
42′ ኤልያስ ማሞ በጊዮርጊሶች ሜዳ አጋማሽ ላይ ከሳልሀዲን ባርጌቾ ጋር ተጋጭቶ በመጎዳቱ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነው።
40′ ናትናኤል ዘለቀ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳልሀዲን ሰይድ በግንባሩ ሲሞክር ሀሪሰን ይዞበታል።
38′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከመጀመሪያው በተሻለ ወደ ተጋጣሚያቸው ግብ ቀርበው ነበር። አብዱልከሪም ኒኪማም ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደላይ ተንስቶበታል።
34′ ኤልያስ ማሞ ከአማኑኤል ዮሀንስ ባጭር ቅብብል የተቀበለውን ኳስ በጊዮርጊሶች የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ግማሽ ጨረቃ ላይ ሞክሮ በጎን ወደውጪ ወጥቶበታል።
29′ ከግራ መስመር ቅዱስ ጊዮርጊሶች ያገኙትን ቅጣት ምት አበባው ቡጣቆ ሲያሻማ አቡበከር ሳኒ በግንባሩ ሞክሮ በግቡ አናት ወጥቶበታል።
28′ ከጎሉ በኋላ ጨዋታው ከመሀል ሜዳ ሲጀመር ሳልሀዲን ሰይድ በቀጥታ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
ጎልልል!!! – ቡና
26′ ኤልያስ ማሞ ከግራ መስመር ያሻማውን ቅጣት ምት ቁመተ መለሎው የመሀል ተከላካይ ኢኮ ፌቨር በግንባሩ አስቆጥሯል።
25′ ቡናማዎቹ በኳስ ቁጥጥር እና ቶሎ ቶሎ ወደግብ በመድረስ የተሻሉ ሆነዋል ነገር ግን የጊዮርጊሶችን ተከላካይ ክፍል ማለፍ አልቻሉም
21′ ኤልያስ ማሞ ከመሀል የተላከለትን ኳስ በግንባሩ አብርዶ ከ 16.50 አካባቢ ቢሞክርም በጊዮርጊስ ጎል ቀኝ በኩን ወጥቶበታል።
19′ ያቡን ዊልያም ከመልሶ ማጥቃት ያገኛትን ኳስ በግራ በኩል ይዞ ገብቶ በቀጥታ ወደግብ ቢሞክርም በግቡ አናት ወጥቶበታል። የጨዋታው የመጀመሪያ አስደንጋጭ ሙከራ።
ቢጫ ካርድ!!
15′ አበባው ቡጣቆ በ እያሱ ታምሩ ላይ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።
13′ ጨዋታው መሀል ሜዳ ላይ በሚቆራረጡ ቅብብሎች እና ርቀት ባላቸው ቅጣት ምቶች ታጅቦ ቀጥሏል
9′ አማኑኤል ከ ጊዮርጊሶች ሳጥን ውስጥ በቀጥታ ቢሞክርም አጠገቡ የነበረው ሳልሀዲን ባርጌቾ ተደርቦ አውጥቶበታል። ጨዋታው በምዕዘን ምት ቀጥሏል።
8′ ሀሪሰን የለጋውን ኳስ ሳላዲን ባርጌቾ መሀል ሜዳ ላይ በደረቱ አብርዶ ሀሪሰን ጎሉን ከመሸፈኑ በፊት በቀጥታ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡
5′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስ ቁጥጥር በቅዱስ ጊዮርጊሶች ሜዳ ላይ አድልቶ እየተካሄደ ነው
ተጀመረ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናው ያቡን ዊልያም አማካይነት ተጀምሯል፡፡
በስታድየሙ ሁሉም መቀመጫዎች የመተላለፊያ ደረጃዎችን ጨምሮ በደጋፊዎች ተሞልተዋል፡፡
ስታድየሙ ከ 8:00 ጀምሮ የሞላ ሲሆን ተጨዋቾቹ በደጋፊዎች ዜማ ታጅበው ካሟሟቁ በኃላ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል፡፡
ኢትዮጽያ ቡና አሰላለፍ
99 ሀሪሰን ሄሱ
18 ሣእለአምላክ ተገኝ — 16 ኤፍሬም ወንድወሰን — 4 ኤኮ ፌቨር — 13 አህመድ ረሽድ
9 ኤልያስ ማሞ — 25 ጋቶች ፓኖም– 8 አማኑኤል ዮሐንስ
24 አስቻለው ግርማ — 28 ያቡን ዊልያም — 14 እያሱ ታምሩ
ተጠባባቂዎች
50. ጆቤድ ኡመድ
5. ወንድይፍራው ጌታሁን
17. አብዱልከሪም ሀሰን
7. ሣዲቅ ሤቾ
11. ሳሙኤል ሳኑሚ
19. አክሊሉ አለሙ
27. ዮሴፍ ዳሙዬ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
30 ሮበርት ኦዶንካራ
15 አስቻለው ታመነ – 13 ሳላሀዲን ባርጊቾ – 23 ምንተስኖት አዳነ – 4 አበባዉ ቡጣቆ
24 ያስር ሙጌርዋ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 27 አብዱልከሪም ነኪማ
10 ራምኬል ሎክ – 7 ሳላዲን ሰኢድ – 18 አቡበከር ሳኒ
ተጠባባቂዎች
1 ፍሬው ጌታሁን
3 መሀሪ መና
2 ፍሬዘር ካሳ
12 ደጉ ደበበ
19 አዳነ ግርማ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
20 ዘካሪያስ ቱጂ