አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ እና ጌታነህ ከበደ ቅጣት ተላልፎባቸዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች ፈጽመዋል ባላቸው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ፣ ጌታነህ ከበደ እና ኄኖክ አዱኛ ላይ ቅጣት አስተላልፏል፡፡


አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ

የመቐለ ከተማው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ክለባቸው ባለፈው እሁድ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ቡድናቸውን ከሚመሩበት ክልል ወጥተው ወደ ተጋጣሚ አሰልጣኞች በመሄድ የሲዳማ ቡናው ምክትል አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ስለመሳደባቸው በጨዋታ አመራሮች በቀረበው ሪፖርት መሰረት በቀጣይ 5 ጨዋታዎች ቡድኑን እንዳይመሩ ቅታት ተላልፎባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 4ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡

ጌታነህ ከበደ

ደደቢት በጅማ አባ ጅፋር በተሸነፈበት ጨዋታ ኄኖክ ኢሳያስን በክርኑ ተማትቶ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣው ጌታነህ ከበደ የ 4 ጨዋታዎች ቅታት ተላልፎበታል፡፡ 4ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትም የውሳኔው አካል ነው፡፡

ኄኖክ አዱኛ

የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር ተከላካይ ከደደቢት በተደረገው ጨዋታ የተጋጣሚን ግልፅ የጎል ማስቆጠር እድል በእጁ በማውታት በማምከኑ በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ መውታቱ የሚታወስ ሲሆን 1 ጨዋታ እና 4ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *