ደቡብ ፖሊስ ሁለተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

በትላንትናው ዕለት አንድ ተጫዋች በማስፈረም ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ የገባው ደቡብ ፖሊስ ዛሬ አንድ ተጫዋች አስፈርሟል። 

ናትናኤል ጌታሁን ወደ ቀድሞ ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር አጠናቋል። የቀኝ መስመር ተከላካዩ ናትናኤል ከሶስት ዓመት በፊት ደቡብ ፖሊስን ለቆ ወደ ወልቂጤ ካመራ በኋላ በ2009 ወደ ደቡብ ፖሊስ ተመልሶ ተጫውቷል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ በሀላባ ከተማ በማሳለፍ በድጋሚ ወደ ሀዋሳው ክለብ በመመለስ የአንድ ዓመት ኮንትራት መፈራረም ችሏል።

ደቡብ ፖሊስ ከናትናኤል ፊርማ በተጨማሪ የሁለት ተጫዋቾችን ውል ማደሱን አስታውቋል። የግራ መስመር ተከላካዩ አየለ ተስፋዬ እና ተከላካዩ ደረጄ ፍሬው በአንድ ዓመት ውላቸውን ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።

በተያያዘ ዜና ደቡብ ፖሊስ የ2011 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅቱን መስከረም 10 በይርጋለም ፖሊስ ማሰልጠኛ እንደሚጀምር ታውቋል።