ሙሉዓለም ረጋሳ ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቷል

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ደቡብ ፖሊስ በዝውውር መስኮቱ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን በመቀጠል አንጋፋው አማካይ ሙሉዓለም ረጋሳን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል። 

ሙሉዓለም ረጋሳ በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ከሚጠቀሱ የምንግዜም ምርጥ አማካዮች አንዱ ሲሆን በ1989 ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ እስከ 2000 ድረስ በነበረው ቆይታ ስድስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። ከነዚህ መካከልም ሦስቱን በአምበልነት ያነሳቸው ነበሩ። ሙሉዓለም ከፈረሰኞቹ ጋር ከተለያየ በኋላ በ2001 ወደ ሰበታ ከተማ ሲያመራ ከዚያም በኢትዮጵያ መድን ቆይታ አድርጎ ከእግርኳስ ርቆ ከቆየ በኋላ በ2010 ዳግም ተመልሶ በሀዋሳ ከተማ መልካም የውድድር ዓመትን ማሳለፍ ችሏል። 

ከግማሽ በላይ ስብስቡን በአዲስ ተጫዋቾች የሞላው ደቡብ ፖሊስ ካስፈረማቸው መካከል የቀድሞ የሙሉዓለም የቡድን አጋር የነበረውና ቅዱስ ጊዮርጊስን ሲለቅ በአምበልነት የተካው ሳምሶን ሙሉጌታን አንዱ ነው። 

ደቡብ ፖሊስ የመጀመርያ የሊግ ጨዋታውን ከመከላከያ ጋር እሁድ ጥቅምት 25 ሀዋሳ ላይ ያደርጋል። 


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ