” ኢትዮጵያ ቡናን ማገልገል ናፍቆኛል” ተመስገን ካስትሮ 

በመጀመርያው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከወራት በፊት ኢትዮጵያ ቡና ከጅማ አባጅፋር ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ የመጀመርያው አጋማሽ ላይ ነበር ተመስገን ካስትሮ ከፍተኛ የጉልበት ጉዳት ያስተናገደው። ያለፉትን ሁለት ወራት በእግሩ ላይ በተገጠመው ጀሶ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው ተመስገን አሁን ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ለሶከር ኢትዮጵያ ይህን ተናግሯል።

” ለሁለት ወራት እግሬ ላይ የቆየው ጀሶ አሁን ተነስቶልኛል። የጉልበቴ ሁለት ጅማቶች ላይ የመሰንጠቅ ጉዳት ነበር ያጋጠመኝ። አሁን ዶክተሮች እንደነገሩኝ ከሆነ ጉዳትህ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ በመሆኑ ከአንድ ወር በኃላ ልምምድ መጀመር ትችላለህ ብለውኛል። ፈተኛ የሆነ ጊዜ ባሳልፍም አሁን ባለው ነገር ደስተኛ ነኝ። ከጉዳቴ በቶሎ አገግሜ ኢትዮጵያ ቡናን ማገልገል ናፍቆኛል” ብሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *