ወልቂጤ ከተማ የዲሲፕሊን ቅጣት ተላለፈበት

ባሳለፍነው ሳምንት የካ ክፍለ ከተማ ከወልቂጤ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የዲሲፒሊን ግድፈት አሳይቷል በሚል ፌዴሬሽኑ ቅጣት አስተላልፎበታል።

በምድብ ለ 12ኛ ሳምንት ኦሜድላ ሜዳ ላይ የካ ክፍለ ከተማ ከወልቂጤ ያደረጉት ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ የወልቂጤ ደጋፊዎች ከፀጥታ አካላት ጋር ግጭት መፍጠራቸው ይታወቃል። ጉዳዩን ሲመለከተው የቆየው የዲሲፕሊን ኮሚቴም ጥፋተኛ ነው ባለው የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ማስተላለፉን ለክለቦቹ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። በዚህም መሠረት የ100,000 ብር ቅጣት እና ሦስት የሜዳው ጨዋታዎችን ከከተማው 200 ኪ/ሜ ርቀት እንዲጫወት ተወስኖበታል።

የቅጣት ውሳኔዎቹ የሚከተሉትን ይመስላሉ፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡