የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች በድጋሚ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገቡ

ውል ያላቸውና ያጠናቀቁ የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ፌዴሬሽኑ በጥብቅ የወሰነው ውሳኔ ተፈፃሚ አልሆነም በማለት በድጋሚ የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ

አስራ ስድስት የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች የአምስት ወር እና የሦስት ወር ደሞዝ አልተከፈለንም በማለት ለፌዴሬሽኑ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በጅማ አባጅፋር ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

የጅማ አባጅፋር እግርኳስ ክለብ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ቢገልፅም እስካሁን ምንም ዓይነት የደሞዝ ክፍያ ያልፈፀመልን በመሆኑ ያለብን የቤተስብ ኃላፊነት ከግምት በማስገባት እና ከክለቡ ይልቅ ማስተማመኛችን ፌዴሬሽኑ በመሆኑ ሙሉ ደሞዛችን እንዲከፈለን ሲሉ በድጋሚ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብተዋል።

*ይህን ዘገባ እያጠናከርን ባለንበት ሰዓት በደረሰን መረጃ ጅማ አባጅፋር ክለብ ለእያንዳንዳቸው ተጫዋቾች የአንድ ወር ደሞዝ እንዳስገባላቸው ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ