የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 2-1 ድሬዳዋ ከተማ

በአማኑኤል አቃናው

ዛሬ ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል ሀዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2-1 ከረታበት ጨዋታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ይህንን ብለዋል።

“የድሬዳዋዎች ጥብቅ መከላከል ጨዋታውን ከባድ አድርጎብን ነበር” አዲሴ ካሳ የሀዋሳ ከተማ ዋና አሰልጣኝ

“ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር ፤ በተከላካይ ስህተትም ግብ አስተናግደን ነበር። ከመስመር በተለይም ከዳንኤል ደርቤ የሚነሱ ኳሶች ቆመው ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ዳንኤልን በዘላለም የቀየርነውም ለዛ ነበር። በኳስ ቁጥጥር እና ወደ ፊት በመሄድም የተሻልን መሆን ችለናል። የድሬዳዋዎች ጥብቅ መከላከል ጨዋታውን ከባድ አድርጎብን ቆይቷል። ሆኖም በመጨረሻ ውጤቱን ይዘን መውጣት ችለናል። በቀጣይ የተከላካይ መስመራችንን የተሻለ ለማድረግ እንሰራለን።”

“ራሳችን በሰራናቸው ስህተቶች ግቦች አስተናግደን ተሸንፈናል” ፍስሃ ጥዑመልሳን – ድሬዳዋ ከተማ ም/አሰልጣኝ

“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ የደጋፊዎች ውጤትን የመቀበል ሁኔታም እየተመሩም ጥሩ ነበር ፤ ተቃውሞም አላሰሙም። ይህ ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው። ዳኝነቱም መልካም ነበር ፤ ራሳችን በሰራናቸው ስህተቶች ግቦች አስተናግደን ተሸንፈናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ