ድሬዳዋዎች የኮሮና ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል

የድሬዳዋ ስታዲየም ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል ሲደረግ የስፖርት ኮሚሽኑ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድሬዳዋ ከተማዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተጀመረውን እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም የወንድ ቡድኑ የአንድ ወር ደሞዝ፣ ሴቶቹ የግማሽ ወር ደሞዝ በመስጠት ድጋፋቸውን ያሳዩ ሲሆን አሁን ደግሞ በአዲስ መልክ የተገነባው የድሬዳዋ ስታዲየምን ለልይቶ ማቆያነት እንዲውል ወስኗል። በተለምዶ ካታንጋ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በቢሮ አገልግሎት ላይ የነበሩ ክፍሎችም ለማቆያነት የሚውሉ ይሎናል።

በተያያዘ ዜና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሮናን ለመከላከል የ1,000,000 ብር ድጋፍ አበርክቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ