የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እና አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸው ላይ ቅናሽ አደረጉ

የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እና አባላት ከአንድ ወር ደሞዛቸው 40% መቀነሳቸውን ክለቡ አስታውቋል።

የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድን አባላት በኮሮና በሽታ ወረርሽኝ ምክንያት ውድድር ተቋርጦ ክለቡም የስታዲየም ገቢና የተለያዩ የገቢ ምንጮቹ መቋረጣቸውን ከግምት በማስገባት የሚያዝያ ወር ደሞዛቸው 40% እንዲቀንስ ለክለቡ ማስታወቃቸውን ክለቡ ገልጿል።

“ተጫዋቾች እና ኮችንግ ስታፎች ክለባችን በዚህ ሰዓት የፋይናንስ ችግር ይገጥመዋል ብለው በማሰብ ደሞዛቸውን በመለገሳቸው በክለባችን እና በደጋፊዎቻችን ስም ልባዊ ምስጋናችን እናቀርባለን። ” ሲልም ክለቡ አስታውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ