የከፍተኛ ሊግ ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ እና የደም ልገሳ አከናውነዋል

የአቃቂ ቃሊቲ እግር ኳስ ክለብ አባላት የደም ልገሳ ሲያከናውኑ ለገጣፎ ለገዳዲዎች ደግሞ የኮሮና ስርጭትን ለመግታት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ከሰሞኑ በሀገራችን የተከሰተውን የደም እጥረት ተከትሎ ብሔራዊ የደም ባንክ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ደም እንዲለገስ ባደረገው ጥሪ መሰረት የአቃቂ ቃሊቲ የወንዶች ቡድን አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች አባላት ልገሳውን አድርገዋል፡፡

ሌላው የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ ለኮሮና መከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ክለቡ በለገጣፎ ለገዳዲ አካባቢ ስርጭቱን ለመከላከል ለሚደረጉ ተግባራት ለተቋቋመው ግብረ ኃይል ከተጫዋቾችእና ከአሰልጣኝ አባላት የተወጣጣ በድምሩ 81,000 (ሰማንያ አንድ ሺ ብር) የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ