የቡታጅራ ከተማ ክለብ ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ

ከዚህ ቀደም ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል የገንዘብ ድጋፍን አበርክቶ የነበረው የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቡታጅራ ከተማ አሁን ደግሞ የቁሳቁስ ድጋፍን ዛሬ አበርክቷል።

ከአንድ ወር በፊት ከተጫዋቾቹ፣ ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ከክለቡ የቢሮ ሰራተኞች ከሀምሳ አንድ ሺህ ብር በላይ ለግሶ የነበረው የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቡታጅራ ከተማ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት ከተጫዋቾቹ፣ ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ከክለቡ ሰራተኞች በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዛውን ለምግብነት የሚውሉ እንደ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ዱቄት፣ ዘይት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የቡድኑ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች እንዲሁም ደግሞ የቢሮ ሰራተኞች በተገኙበት በክለቡ አሰልጣኝ አስራት አባተ አማካኝነት ለአቅመ ደካሞች እንዲውል ዛሬ ለቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አህመድ ኑሪ አስረክበዋል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ እና ከተጫዋቾቹ ባገኘችው መረጃ መሠረት ሙሉ በሙሉ ለተጫዋቾቹ ክለቡ ወርሀዊ የደመወዝ ክፍያን እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡



👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ