“ከሐምሌ 30 በኃላ የሚሆነውን አብረን እናያለን” አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ

ያለፉትን ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በማሰልጠን የቆዩት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ከሁለት ቀናት በኃላ ሐምሌ ሠላሳ ኮንትራታቸው የሚያበቃ ይሆናል። ፌዴሬሽኑ በበኩሉ የአሰልጣኙን ውል በተለያዩ ምክንያቶች እንደማያድስ በይፋ መግለፁ ይታወቃል። በዚህ መነሻነት አሰልጣኙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስማቸው እየተያያዘ ይገኛል። ስለሚነሳው ጉዳይ እና በቀጣይ የብሔራዊ ቡድን ኮንትራታቸው ካበቃ በኋላ እቅዳቸው ምን ይሆን በማለት ላቀረብንላቸው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል።

“እስካሁን ከማንም ጋር በዚህ ጉዳይ አልተነጋገርኩም። እስከ ሐምሌ ሠላሳ የፌዴሬሽኑ ሠራተኛ ነኝ፤ በዚህ መሐል ከማንም ጋር መነጋገር አልችልም። ከዚህ ክለብ ጋር ተስማምቷል የሚሉ ነገሮችን በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እሰማለው። እኔ ግን በግልፅ ከአንዳቸው ጋር አልተነጋገርኩም። ከካፍ እና ከፊፋ ጋር የምሰራቸው ሥራዎች (የቪዲዮ ኮንፍረሶች) አሉ። እነርሱ ሥራ ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው ያለሁት። በቀጣይ ከፈጣሪ ጋር ማረፊያዬን አሳውቃለው። እዚሁ በሀገሬ እየሰራው የምቆይ ይመስለኛል። ለማንኛውም ከሐምሌ ሠላሳ በኃላ የሚሆነውን አብረን እናያለን።” ብለዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ