ሁለት ተጫዋቾች ለሰበታ ከተማ ለመፈረም ተስማሙ

ያሬድ ታደሰ እና መሳይ ጳውሎስ ለሰበታ ከተማ ለመጫወት ተስማሙ፡፡

ወጣቱ የመስመር አጥቂ ያሬድ ታደሰ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተውን ቡድን የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል፡፡ የቀድሞው የናሽናል ሲሚንት ተጫዋች ከአዳማ ከተማ ዋንጫ እስከ ፕሪምየር ሊጉ ለድሬዳዋ ከተማ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በሁለት ዓመት ኮንትራት መስማማቱን ተከትሎ በሰበታ ከተማ የማጥቃት ኃይሉን ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላኛው የመሐል ተከላካዩ መሳይ ጳውሎስ ነው በዛሬው ዕለት ለሰበታ ፊርማውን ለማኖር የተስማማው። ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አማካኝነት ካደገ በኃላ ባለፉት አራት ዓመታት በሀዋሳ በመጫወት ወጥ አቅሙን ሲያሳይ የነበረ ሲሆን ለአሰልጣኝ ውበቱ አጨዋወት አመቺ ክህሎት ያለው ተጫዋቹ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

ቡልቻ ሹራን፣ ፉአድ ፈረጃ እና ዳንኤል ኃይሉን ከዚህ ቀደም ለማስፈረም የተስማሙት ሰበታ ከተማዎች የአዳዲስ ፈራሚዎቻቸውን ቁጥር አምስት አድርሰዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: