“በጨዋታ ጊዜ አንድን ተጫዋች ለረጅም ጊዜ መከታተል አይቻልም”

ውድድሮች እንዲጀምሩ በተዘጋጀው የመነሻ ሰነድ ላይ የተካተተው “ተጫዋቾችን ለረጅም ጊዜ መከታተል (ማርክ ማድረግ) አይቻለም” የሚለው ነጥብ ትኩረት ሳቢ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮች እንዲጀመሩ የመነሻ ሰነድ አዘጋጅቶ በዛሬው ዕለት ሲ ኤም ሲ አካባቢ በሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል ለክለቦች ማቅረቡ ይታወቃል። በመነሻ ሰነዱም ላይ ውድድሮች እንዲጀመሩ የሚያስችሉ የተለያዩ መዘርዝሮች ቀርበው ውይይቶች ተደርገዋል። ከቀረቡት ዝርዝር መነሻ ሃሳቦች ላይ ከተካተቱት መካከል “ተጫዋቾችን ለረጅም ጊዜ መያዝ አይቻልም” የሚለው ነጥብ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

30 ገፆች ባሉት ይህ ሰነድ ላይ የተካተተው ይህ ሃሳብ እንዴት ይተገበራል፣ እንዴትስ “ጥፋቱን” መቆጣጠር ይቻላል እንዲሁም ይህንን ያጠፋው ተጫዋች ላይ ምን አይነት ቅጣት ይጣልበታል የሚለው ጉዳይ በግልፅ ያልተብራራ ሲሆን አፈፃፀሙ ግን ወደፊት በሚወጣው የውድድር ደምብ ላይ በግልፅ እንደሚብራራ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ