ድሬዳዋ አማካይ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማማ

ብርቱካናማዎቹ የመሀል ሜዳ ተጫዋች የሆነው ሙሉቀን አይዳኝን አራተኛ ፈራሚ ለማድረግ ተስማሙ፡፡

እግርኳስን በድሬዳዋ የጀመረው ይህ አማካይ ለናሽናል ሲሚንት ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ክለቡን ከለቀቀ በኃላ ከ2011 ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ለአዲስአበባ ከተማ በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ድሬዳዋ ተመልሶ በሁለት ዓመት ውል ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ