የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-2 አዳማ ከተማ

ከከሰዓቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ከሱፐር ስፖርት ጋር የነበራቸው ቆይታ ይህንን ይመስላል።

አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለቡድናቸው እንቅስቃሴ

በአብዛኛው የጨዋታው ደቂቃዎች በኳስ እና ቦታ አያያዛችን ጥሩ ነበርን። እንቅስቃሴያችን መልካም በመሆኑም ነው አራት ግቦች ያስቆጠርነው። እርግጥ ነው ኋላ ላይ ትኩረታችን በመቀነሱ ግቦች እንዲቆጠርብን ሆኗል። ነገር ግን በመጨረሻ ጨዋታውን አሸንፈን መውጣት ችለናል።

ስለቡድናቸው የውድድር አጋማሽ ጉዞ

በቡድኑ ውስጥ ብዙ መሻሻሎች አሉ። ብዙ የሚጠበቅብን ከመሆኑም አንፃር ልናሻሽላቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች ነበሩ። የመጀመሪያውን እና የአሁኑን ጨዋታ የተመለከትን እንደሆን ግን ብዙ ለውጦች እንዳሉ መረዳት እንችላለን። በቀጣይም ከየጨዋታዎቹ ሙሉ ነጥቦችን ለማሳካት ጥረታችንን መቀጠል ይኖርብናል።

አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል

ስለጨዋታው

መጀመሪያ ላይ የተቆጠሩት ጎሎች ዋጋ አስከፍለውናል። ከዕረፍት በኋላ ቅያሪ አድርገን ለውጥ አምጥተናል። በጥቃቅን ስህተት ነው ውጤት ያጣነው ፤ ያው እግር ኳስ ነው እንግዲህ።

ስለአራተኛው ጎል ተፅዕኖ

አዎ ፤ እሱ ጎል የነበረንን ተነሳሽነት አውርዶታል። ያው እግር ኳስ ነው። አራትም ቢገባ የመጨረሻው ጎል የልጆቹን አዕምሮ ተፅዕኔ ውስጥ ከቶታል። ማዳን እየቻልን ተደጋጋሚ እንዲህ ዓይነት ጎሎች እየገቡብን ነው። ያው ከስህተታችን ተምረን ለመምጣት እንሞክራለን ፤ ኃላፊነት እንወስዳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ