ኢትዮጵያ ቡና የወሳኝ አማካዩን ውል አድሷል

በአሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች የወሳኝ አማካያቸውን ውል ለአራት ዓመታት ማደሳቸውን አስታውቀዋል።

በዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ ፍክክር እያደረጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በዛሬወ ዕለት የወሳኙን አማካያቸው ታፈሰ ሰለሞንን ውል ማደሳቸው ታውቋል። በኒያላ የእግርኳስ ህይወቱን ጀምሮ ወደ በኤሌክትሪክ፣ አህሊ ሸንዲ እና ሀዋሳ ከተማ በመጓዝ የተቀጠለው ታፈሰ በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን መቀላቀሉ ይታወሳል።

ተጫዋቹ በቡናማዎቹ ቤት ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ውሉሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ከደቂቃዎች በፊት ክለቡ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረትም ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ለቀጣይ አራት ዓመታት (እስከ 2016) ለመቆየት ተስማምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ