በአምላክ ተሰማ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተመረጡ ዳኞች አንዱ ሆኗል

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የእግርኳስ ውድድር ላይ ከሚመሩ ዳኞች አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

በዓለም ዋንጫ፣ አፍሪካ ዋንጫ፣ የዓለም ክለቦች ውድድር እና በአፍሪካ የክለቦች ውድድሮች ላይ የተገኘው ባምላክ አሁን ደግሞ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ እንዲመሩ ፊፋ በዛሬው ዕለት ባሳወቀው የዳኞች ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ” ሁሌም ስጠብቀው እና ሳልመው በነበረው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ሀገሬን በእግር ኳስ ዘርፍ በዳኝነት በመወከሌ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል።” ሲልም ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ተናግሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ