የቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር ደርሷል

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኤርትራ እና ዩጋንዳ ተከትላ ሴካፋ በሚደረግበት ባህር ዳር ከተማ የገባችው ሀገር ቡሩንዲ ሆናለች።

የፊታችን ቅዳሜ እንደሚጀመር የሚጠበቀው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር ተሳታፊዎች ወደ ባህር ዳር ከተማ መግባታቸውን ቀጥለዋል። እስከ ትናንት ማታ ድረስ አራት ሀገራት ባህር ዳር መግባታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የቡሩንዲ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ስፍራው መድረሱ ታውቋል።

በውድድሩ ትኩረት በመስጠት በርካታ ጥምር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ይዞ በሀገሩ ሲዘጋጅ የነበረው ቡድኑ ውድድሩ በሚፈቅደው ህግ መሠረት 23 ተጫዋቾችን ብቻ በመያዝ ወደ ባህር ዳር አምርቷል።