ሁለቱ ወጣቶች በመጨረሻም ለፈረሰኞቹ ፈርመዋል

ከዚህ ቀደም በዘገባችን ገልፀን የነበረው የቸርነት ጉግሳ እና በረከት ወልዴ ዝውውር ተጠናቀቀ፡፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር አመትን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የፈፀመው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ ከመቅጠሩ አስቀድሞ የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ እና አማካዩ በረከት ወልዴ ከጋቶች ፓኖም ቀጥሎ ፈረሰኞቹን ተቀላቅለዋል፡፡

ከወላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን በ2008 ከተገኘ በኃላ በወጥነት ለስድስት ዓመታት በዋናው ቡድን መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ እና በተመሳሳይ እንደ ቸርነት ሁሉ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በጦና ንቦቹ መለያ የደመቀው የተከላካይ አማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ በረከት ወልዴም ለሁለት ዓመት በይፋ ፈረሰኞቹን ተቀላቅለዋል፡፡