የጂቡቲ ብሔራዊ ቡድን አባላት የባህር ዳርን ምድር ረግጠዋል

በምድብ ሦስት የሚገኘው የጂቡቲ ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር ከተማ መድረሱ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታ የሚከፈተው 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከነገ በስትያ ይጀመራል። የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራትም ውድድሩ ወደሚደረግበት ባህር ዳር ከተማ እየገቡ መሆኑ ሲታወቅ ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የጂቡቲ ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር መድረሱ ታውቋል።

ከኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር የተደለደለችው ጂቡቲ ከምድቧ 2ኛ ከአጠቃላይ ተሳታፊ ሀገሮች ደግሞ 6ኛዋ ባህር ዳር የደረሰች ሀገር ሆናለች። ብሔራዊ ቡድኑም በፓልም ፓላስ ሆቴል እንዳረፈ ተጠቁሟል። ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የጂቡቲን ጨምሮ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኤርትራ፣ ዩጋንዳ እና የቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድኖች ባህር ዳር ከተማ ደርሰዋል።