ቡናማዎቹ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ከደቂቃዎች በፊት አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

እስካሁን የአራት ተጫዋቾችን ዝውውር የጨረሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከደቂቃዎች በፊት ከቅዱስ ጊዮርጊስ የለቀቀውን አቤል እንዳለን በሦስት ዓመት ውል ማስፈረማቸው ታውቋል።

ከ2009 ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት የውድድር ዓመታት ለደደቢት ግልጋሎት የሰጠው አቤል በተሰረዘው የውድድር ዘመን ቅዱስ ጊዮርጊስን መቀላቀሉ አይዘነጋም። ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ሌላኛውን የመዲና ክለብ (ኢትዮጵያ ቡና) ለመቀላቀል ፊርማ ማኖሩን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።