የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ሀዲያ ሆሳዕና

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ያለግብ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የተደመጠው የአሰልጣኞች አስተያየት እንዲህ ይነበባል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለጨዋታው

” ከባድ ጨዋታ ነበር። ይህ እንደሚገጥመን አውቀነው ነበር። ከባድ ቡድን ነው ሁሉ ነገራቸው ጠንክሮ ነው የመጣው። እኛ ላይ ሁሉም ቡድን እንደአዲስ ሁሌም ጠንክሮ እንደሚመጣ እናውቃለን። ያ ነገር ነው ሜዳ ላይም የገጠመን።

ቡድኑ በአጨዋወት ለውጥ ምላሽ ስለመስጠቱ

“አማራጭ ወስደን ነበር። የልጆቻችን ሙሉ ለሙሉ ያላቸውን አቅም ስላልተጠቀሙ ነው እንጂ እነሱ እንደዚህ እንደሚጫወቱ መጀመሪያም አውቀን ነበር የመጣነው። መስመሮቹን በደንብ ለመጠቀም ነበር የመጣነው። ያው ሁሌም ጨዋታ አንድ ዓይነት አይሆንም። ልጆቼ ብዙ ጉልበት ስላወጡ ይመስለኛል ብዙ ምቾት አልተሰማቸውም ዛሬ።

ስለተጋጣሚ አቀራረብ

“እንደዚህ እንደሚጫወቱ እናውቅ ነበር። በዚህም ነበር የሰራነው ፤ እንደገና ደግሞ ከባድ ጨዋታ እንደነበር እናውቃለን። ግን በእኛ አቅም ሙሉ ለሙሉ ያለንንን ነገር በትክክል ስላላደረግን 0-0 ልንወጣ ችለናል።”

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለጨዋታው

“በእርግጥ ዛሬ የተጫወትነው ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነው። ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቀን ግልፅ ነው። ሆኖም ግን ያሰብነውን አሳክተናል። ምክንያቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን 4 ፣ 2 ፣ 4 ጎሎች እያገባ ነው እዚህ የደረሰው። ትንሽ ከባድ ነበር። ሰሞኑን ስንመለከት የነበረው ይህንን ስለሆነ ቢያንስ ትንሽ ወረድ ብለን እነሱን ክፍተት ከልክለን ለመጫወት ነበር። አንድ ነጥብ አግኝተናል ፤ ተሳክቶልናል። ልጆቼ ደግሞ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል። በጣም አሪፍ ነበር ፤ ደስ ብሎኛል።

ይዘው ስለገቡት አጨዋወት

“የጊዮርጊስ አጥቂዎች እንደሚታወቀው በጣም ፈጣኖች ፣ በጥራትም ትልልቅ ተጫዋቾች ናቸው። ክፍተት እና ኳስ ካገኙ መጨረስ የሚችሉ በመሆኑ ያንን ክፍተት መከልከል ነበር። ለማሸነፍ ከፈለክ ደግሞ ተቃራኒ ቡድኖች የሚጫወቱበትን መንገድ ከልክለህ ነው አንተ ማሸነፍ የምትችለው። ያንን ከልክለን ነው ባገኘነው አጋጣሚ ለመጠቀም ያሰብነው። የመጀመሪያው ተሳክቶልናል ሁለተኛውን አልተጠቀምንም ፤ ያሰብነውን አንድ ነጥብ ግን አሳክተናል።

ስለውጤቱ ተገቢነት

“ብዙ ለፍተናል። ጊዮርጊስ ጠንካራ ቡድን ነው ብዬሀለው። ክፍተት ብንሰጣቸው አንድ ሁለት ሦስት አራት የለመዱትን ግብ እንደሚያገቡ ግልፅ ነው። በዛ ላይ ነው ስንሰራ የነበረው ፤ የሰራነውን ደግሞ ተግባራዊ አድርገናል። ተገቢ ነው ብዬ ነው የማስበው።”