ድሬዳዋ ከተማ በስምምነት ከአምበሉ ጋር ተለያቷል

በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ የቀላቀለው ድሬዳዋ ከተማ ከአምበሉ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ ዘንድሮ ዓመት የተለያዩ ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ በመቀላቀል በአማራ ጣና ዋንጫ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ከአማካይ ተጫዋቹ ዳንኤል ደምሱ ጋር በስምምነት መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

በወልድያ፣ በኢትዮጵየ ቡና፣ በመቐለ ሰባ አንድርታ እና በሌሎች ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ዳንኤል ክለቡን በአምበልነት መምራቱ ሲታወስ ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት እየቀረው ነው በስምምነት የተለያየው።

ድሬዳዋ ከተማ ከሰሞኑ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋርም በስምምነት ይለያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል።