ንግድ ባንክ የአማካዩን ውል አድሷል

ከቀናት በፊት የአራት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሶ አንድ አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ንግድ ባንክ ዛሬ ደግሞ የአማካዩን ቆይታ ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

የወቅቱ የሊጉ ዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት የብዙዓየሁ ታደሰ፣ ሰናይት ቦጋለ፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና አረጋሽ ካልሳን ውል ለተጨማሪ ዓመት ማራዘሙ ይታወቃል። ለ2015 የሊጉ ውድድር በቀጣዩ ሳምንት አጋማሽ ዝግጅቱን ሀዋሳ ላይ የሚጀምረው ክለቡም በዛሬው ዕለት ደግሞ የተጨማሪ አንድ ተጫዋችን ውል ማደሱ ታውቋል።

ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በክለቡ ለመቆየት ፊርማዋን ያኖረችው ተጫዋች እመቤት አዲሱ ናት። የቀድሞ የአርባምንጭ ከተማ እና መከላከያ አማካይ 2012 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መቀላቀሏ ይታወሳል። በክለቡ በአጠቃላይ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ለመቆየትም ዛሬው ዕለት ፊርማዋን በይፋ አኑራለች።