የነገውን የባህር ዳር ከነማ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

በአዲስ አበበ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በባህር ዳር ከተማ እና አዛም መካከል የሚደረገውን ወሳኝ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት መደረግ እንደጀመሩ ይታወቃል። በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ በሁለተኛው አህጉራዊ የክለቦች ውድድር የሚሳተፈው ባህር ዳር ከተማ ነገ 10 ሰዓት በመዲናችን አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የታንዛኒያውን ክለብ አዛም ይገጥማል።

ይህንን ጨዋታ እንዲመሩም ሱማሊያዊያን ዳኞች እንደተመደቡ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ጨዋታውን በመሐል አልቢትርነት ሀሰን መሐመድ ሀጂ ሲመሩት ኑር አብዲ መሐመድ እና መውሊድ ራጂ ዓሊ በረዳትነት እንዲሁም አህመድ ሀሰን ሁሴን አህመድ በአራተኛ ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።