አቤል ያለው የግብፁን ክለብ ተቀላቅሏል

ከቀናት በፊት እንዳስነበብናችሁ የፈረሠኞቹ አጥቂ የሆነው አቤል ያለው የግብጹን ዜድ መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ዘንድሮ ከታች በማደግ በግብፅ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተሳተፈ ያለው ክለብ የቅዱስ ጊዮርጊሱን አጥቂ ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር ተስማምቶ የክለቡ ምላሽ እንደሚጠበቅ አስነብበናችሁ ነበር።

ሆኖም ባደገበት ዓመት የግብፅ ፕሪምየር ሊግን በ19 ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ዜድ ክለብ ኢትዮጵያዊውን የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ አቤል ያለውን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱ ከተሰማ ጀምሮ በስፖርት ክለቡ ፣ በፌዴሬሽን ሰዎች እና በተጫዋቹም ጠንካራ ጥረት መሳካት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።