የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመልስ ጨዋታ አይካሄድም

በ2018 ኬንያ ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ሀገራት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከጅቡቲ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ጨዋታ ወደ ጅቡቲ በማቅናት 5-1 አሸንፋ መመለሷ ይታወሳል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ  ጨዋታ የፊታችን እሁድ ሃዋሳ ላይ ይደረጋል ተብሎ መርሃ ግብር ቢወጣለትም የጅቡቲ እግር ኳስ ፌደሬሽን ብሄራዊ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ እንደማይልክ ትላንት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በላከው ደብዳቤ የገለጸ ሲሆን ትላንት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጅቡቲ የመጣውን ደብዳቤ ተመልክቶ ለካፍ በላከው ደብዳቤ ስለ ጉዳዩ በማስረዳት ጨዋታው እንደማይከናወን ማረጋገጥ ቻሏል፡፡

ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ የጅቡቲ እግር ኳስ ፌደሬሽን የመልስ ጨዋታውን አላከናውንም በማለቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለዳኞች ትራንስፖርት እና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ያወጣውን ወጪ የጅቡቲ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚሸፍን ሲሆን በቀጣይም ካፍ በጅቡቲ ላይ ከእሁዱ ጨዋታ ፎርፌ በተጨማሪ ቅጣቶችን እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ተከታዩ ዙር ማለፉን ተከትሎ በቀጣይ ዙር በተመሳሳይ ሱዳንን በፎርፌ ካሸነፈችው ቡሩንዲ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *